ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በጠራው ስብሰባ ላይ ያደረገው ንግግር ሙሉ ቃል

“አማራ በብሔር መደራጀት ችግር የወለደው ቢሆንም አማራ በብሔረ መደራጀት መብታችን ነው፡፡ የማንንም ፍቃድ አያስፈልገንም፡፡ ሀቁ ይህ እንደሆነ የአማራ ህዝባችን ከስሜት ነፃ በሆነ አስተምህሮ በመስጠት ህዝቡን ጠንካራ አቋም እንዲይዝ በማድረግ ራሱን ከማንኛውም የዘር ጥቃት እንዲከላከል ማድረግ”

~ህወሓት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ብሔርተኝነት አለመመለሱ ከጊዜ በኋላ ውጤቱ ቀሪው ኃይል በታሪክ ሊነግረን ይሆናል፡፡ ህወሓት የአማራ ህዝብ ጥያቄ ላለመመለስ ጦርነት ከመረጠ በአማራ አሸናፊነት እንደሚደመደም አትጠራጠሩ፡፡ ህወሓት የአማራ ህዝብ ጥያቄ በሰላም ከመለሰ ግን አሸናፊም ተሸናፊም አይኖርም በኢትዮጵያዊነታችን በጋራ እንኖራለን፡፡

~የአማራ ህዝብ የተለያዩና ብዙ ድርጅቶች ለችግራችን መፍትሄ አይደሉም፡፡ የአማራ ህዝብ የሚያስፈልገን አንድ ወይም ሁለት ጠንካራ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ብቻ ነው የሚያስፈልጉን እንዲህ ከሆነ ጉልበትም አቅምም እንዲፈጥር አማራ ይረዳል፡፡

ሙሉ ንግግሩ ከስር ይገኛል!

ቀን 08/01/2011ዓ.ም

ቀጣይ መስራት የሚገባን እና ሊገጥሙን የሚችሉ ችግሮችና መፍትሔዎች

1. መስራት የሚገባን

የአማራ የማንነት ጥያቄያችን አወንታዊ መልስ እንዲያገኝ በህጋዊ መልክ ተስፋ ሳንቆርጥ እስከ መጨረሻ መታገል የወልቃይት ጠገዴ የአማራ የማንነት ጥያቄ የመላ አማራ ህዝብ ጥያቄ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

የመላ አማራ ህዝብ ጥያቄ ብቻ ሣይሆን የመላ አማራ መንግስትና ድርጅት ጥያቄ እንዲሆን አጥብቀን መታገል ይገባናል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የአማራ የማንነት ጥያቄ መንግስት ህግና እውነትን ይዞ በፍትሃዊነት ጥያቄውን እንዲመልሰው ወሳኙ የአማራ ህዝብ ስለሆነ አማራ በጠንካራ ብሔርተኝነት ተደራጅቶ መታገል ይገባዋል፡፡

እንደ አማራ ብሔር ተወላጆች መጠን እኛ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴና መላ የወልቃይት ጠገዴ ህዝባችን ጋር ከመላ የአማራ ሕዝብ ጐን ተሰልፈን ብሔራዊ ማንነታችንና ክብራችን ለማስመለስ አሁንም ጠንክረን እንታገላለን፡፡

የአማራ ብሔርተኝነት በማጠናከር ጠንካራ አገር እንድትኖረን ለኢትዮጵያ አገራችን በሙሉ ልብ እንታገላለን፡፡ የአማራ ብሔርተኝነት በማጠናከር ጠንካራ አገር እንድትኖረን ለኢትዮጵያ አገራችን በሙሉ ልብ እንታገላለን፡፡ የመላ የአማራ ህዝብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንዲሁም ማህበራዊ እኩልነት የሚያረጋግጥ መንግስት እንዲኖረን አጥብቀን ልንታገል ይገባል፡፡

የአንድ ብሔር አንድነትና ፍቅር የሚመሰረተው ከአንድ ቤት ቤተሰብና ከቀበሌ ነው። የአንድ አገር አንድነትና ፍቅር የሚመሰረተው ከአንድ ዞን እና ከአንድ ብሔር ነው፡፡ ለዚህ ነው ጠንካራ ኢትዮጵያ ለመፍጠር ጠንካራ የአማራ ብሔረተኝነት እንፍጠር የምንለው፡፡

አማራዎች ባለፉት ሃያ ሰባት/27/ ዓመታት ብዙ ግፍና በደሎች አሳልፈናል፡፡ እንድንገደል፣ እንድንታሰር፣ እንድንሰደድ፣ ተፈጥሮአዊ ሃብታችን እና መሬታችን እንድንዘረፍ ዋና ምክንያት ምክንያታዊ ያልሆነ አንድነት እየሰበክን አንዲት ኢትዮጵያን ሳናገኝ አማራ ራሱን ሳያድን ለከፍተኛ ጥቃት ተዳርጓል፡፡ ስለሆነ በብሔር ያለ መደራጀታችን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈለን ምስክር አያስፈልገንም፡፡

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጎንደር ላይ የተሳካ ስብሰባ ካሄደ

ስለዚህ አማራ በብሔር መደራጀት ምንም አማራጭ የሌለው ሃሣብ እንደሆነ እናምናለን፡፡ አማራ በጠንካራ ብሔርተኝነት ካልተደራጀ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የአማራ የወሰን ጥያቄዎች እንደማይመለሱ እርግጠኞች ነን፡፡ መሰረታዊ የማንነት ጥያቄ፣ የወሰን ጥያቄ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እኩልነት እንዲመለስ ወንድ ሴት፣ ወጣት ሽማግሌ፣ ሙስሊም ክርስቲያን ሳንባባል ቅማንት፣ አገው፣ ኦሮሞ፣ ስናሻ ሳንባባል በአንድ አማራነት ስር ተደራጅተን በሚለያዩን ተከባብረን በሚያመሳስሉን ተቀራርበን በመስራት አንድ አማራ ድርጅት ልንመሰርት ይገባል፡፡ አንድ አማራ፣ አንድ አገው፣ አንድ ኦሮሞ፣ አንድ ቅማንት፣ ሲጠቃ ሲበደል አንድ አንድ አማራ ተደራጅተን ጥቃቱን ልንከላከል እና ልናድነው ይገባል፡፡

የአማራ ጠላቶች የሚያመሳስሉን ሳይሆን ልዩነታችን በጥላቻ እያሰፉ እርስ በእርሳችን እንድንጋደል፣ እንድንጠፋፋ በሚያረጉት ሴራ በጋራ በንቃት ልንከላከል ይገባል፡፡ አማራ የሚያጠቃን ውጫዊ ሣይሆን ውስጣዊ አለመግባባት ካለ ብቻ ነው፡፡

2. የአማራ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎች እንዳይመለሱ የሚገጥሙን ችግሮች:_

1. ማንነት ማለት ምን ማለት ነው ትክክለኛ ትርጉም ካለመረዳት የማንም የፖለቲካ ነጋሴ ሰለባ የመሆን አቋም የማጣት ሁኔታ፣

2. ምክንያታዊ የብሔር መደራጀትና ምክንያታዊ የአገር አንድነት በትክክል ለያይቶ ካለመረዳት ከነፈሰው የመንፈስ ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል፡፡

3. ክብረኛ በመሆን እኔ ያልኩትን ስሙ የማለትና ልታይ ልታይ በማለት በተለየ በወጣቱ ክፍል አለመግባባት ሊፈጠር ይችላል፡፡

4. የማንነት ጥያቄና የብሔርተኝነት አደረጃጀት ለግል ጥቅም ማራመጃ የመጠቀም የማንነት ጥያቄው ሆነ የብሔር አደረጃጀቱ በግዚያዊነት የግል ጥቅም ምንም የሌለው ተጠቃሚነቱ የጋራና የረጅም ጊዜ ሁኖ ሲያገኘው ተስፋ የመቁረጥ ከዚህ በተነሣ ትግሉን ከማኽል መንገድ ትቶ የመሔድ ለሚታገድ ታጋዮች የማጥላላት ጥቅም ወደ አለበት የመንሸራተት ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል፡፡

5. ህወሓት የትግራይ መንግስት የአማራ ደካማ ጐን እያየ ዘርና ጐሣን መሰረት አድርጐ አማራ በብሔር እንዳይደራጅ ከፍተኛ ገንዘብ በማፍሰስ አንድ እንዳንሆን በራሳችን ሰው ወዳጅ እየመሰለ እርስ በርሳችን ሊያጋጨን ይችላል፡፡

6. “የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ትግራይም አማራም አይደለም ወልቃይት ራሱ የቻለ ህዝብ ነው የወልቃይት ራስ ገዝ ነው የምንፈልገው” የሚሉ ኮሚቴ በማቋቋም የወልቃይት ህዝብ በማደናገር ብሎም ለፌዴራል መንግስት ግራ በማጋባት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንነት ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንዳያገኝ ማዘግየት፡፡ ሁለቱ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከአማራ ህዝብ በመነጠል ማንነትና ታሪክ አልባ በማስቀረት በሁለት ዱላ እንዲመታ የተለያየ ሴራ ሊፈጥር ይችላል፡፡

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጎንደር ላይ የተሳካ ስብሰባ አካሄደ

7. አሁን ያሉ የአማራ ድርጅቶችና የአንድነት ድርጅቶች አባላት ምክንያታዊ የሆነ ፖለቲካ ከመከተል ይልቅ ጭፍን የሆነ የቲፎዞ ፖለቲካ በመከተል ተቀራርበን በሃሣብ ከመመካከር ይልቅ በሩቅ ሁኖ አንዱን የአንዱን ስም በማጥፋት እኔን ስሙኝ የማለት ወቅታዊ የህዝብ ስሜትን በማየት ለጊዜያዊ የፓርቲ ጥቅም በመሮጥ የህዝብ መሠረታዊ ጥያቄ የመርሳትና ህዝብን ግራ የማጋባት ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል፡፡

መፍትሄዎች

የማንነት ትርጉም ካለመረዳት የሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄው ማህበረሰቡን በተለያየ መልኩ ማስተማር ማንነት ማለት ቋንቋ፣ ባህል፣ ስነ-ልቦና፣ የመሬት ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥና ታሪክ እንደሆነ ቋንቋ በጉርብትና፣ በትምህርት፣ በስደትና በእናት አባት የሚገኝ ሲሆን ትክክለኛ የማንነት ቋንቋየ የሚባል ሐዘንና ደስታህን የምትገልጽበት ቋንቋ ሲሆን የማንነት ቋንቋየ ማለት እንደሆነ ማስተማር አለብን፡፡

ምክንያታዊ የብሔር አደረጃጀትና ጥቅሙን ካለመረዳት አማራ በብሔር መደራጀት ችግር የወለደው ቢሆንም አማራ በብሔረ መደራጀት መብታችን ነው፡፡ የማንንም ፍቃድ አያስፈልገንም፡፡ ሀቁ ይህ እንደሆነ የአማራ ህዝባችን ከስሜት ነፃ በሆነ አስተምህሮ በመስጠት ህዝቡን ጠንካራ አቋም እንዲይዝ በማድረግ ራሱን ከማንኛውም የዘር ጥቃት እንዲከላከል ማድረግ፡፡ አማራ ሲኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች አማራ ከለለ ኢትዮጵያም አትኖርም በማለት ለአማራ ህዝብ እውቅናና ህልውና የሚያምን መንግስትና አገር እንድትኖረን አበክረን መታገል፡፡ የአማራ ህዝብ መሠረታዊና ጊዜያዊ ጥያቄዎችን ለማህበረሰቡ አብራርቶ ማስረዳት፡፡
ክብረኛ የመሆን አዝማሚያ መድሃኒቱ ህዝብና አገርን ማዕከል በማድረግ የግል ክብርና እኔ ያልኩት ብቻ ስሙ የሚል አመለካከት ጠቃሚ እንዳልሆነ የማያግባባ እንደሆነ አይተን ለሰው ልጅ አክብሮት ትህትናን በማሳየት እርስ በእርሳችን በመደማመጥ ለህዝባችን ዘላቂ ጥቅም የሚያመጣ አቅጣጫ መከተል፡፡

የማንነት ጥያቄና የብሔርተኝነት አደረጃጀት በትክክለኛ መንገድ ከማስኬድ ይልቅ ለግል ጥቅም ማስገኛ የምንሮጥ ከሆነ ትግሉን ከመንገድ ጥለነው ተስፋ በመቁረጥ የምንሄድ ከሆነ የመገዛ የራሳችን ህዝብ ትላንትና ከገጠመን ግፍና በደል የነገው ጥፋትና ግፍ ሊያመዝን ይችላል ስለሆነ “ገንዘብ ጠፊና አላፊ ነው” በሚል አመለካከት ለብሔራዊ ማንነታችን እና ክብራችን በፅናት ልንታገል ይገባል፡፡

ህወሓት የትግራይ መንግስት ዘርና ጐሳን መሠረት አድርጐ አማራ አንድ እንዳይሆን ከፍተኛ በጀት በመመደብ እርስ በእርሳችን ለማናቆር የሚያደርገው ሴራ በትክክል በመረዳት ዘርና ጐሣ ሳንለይ በእውነትና በሀቀኝነት ለአንድ አማራ ለአንዲት ኢትዮጵያ ልንታገል ይገባል፡፡ ህወሓት የትግራይ ተወላጆች በሁለት አቅጣጫ አሰልፎታል አንዱ ግልፅ የሆነ ደጋፊ የአባልነት ካርድ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ድብቅ ደጋፊ የአማራ መታወቂያ በማስያዝ ግማሹ የህወሓት ጠላትና ተቃዋሚ በማስመሰል በአማራ ድርጅቶችና ተቋማት በገንዘብ እንዲቀጠሩ በማድረግ ከፍተኛ የስለላና የደህንነት ስራ እንዲሰሩ በማድረግ የአማራ መንግስትና ህዝብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በመቆጣጠር የህወሓት የጀርባ አጥንት ሆነው እንዲያገለግሉ የትግራይ ተወላጆች አሰላለፍ ፈጥሯል፡፡

ለዚህ መድኃኒቱ የትግራይ ተወላጆች በአማራ ህዝብ ላይ እንደ ካሁን ቀደሙ ሁሉን ነገር በየዋህነት ከፍተን መስጠት ማቆም ነው፡፡ ህውሓት የቀማንን ማንነትና መሬት እስከሚመልስ ድረስ የትግራይ ተወላጆች በፖለቲካ አስተዳደር፣ በፀጥታ አስተዳደር፣ በደህንነት ስልጣን፣ ለሕዝብ ደህንነት አስጊ በሆኑ ተቋማት እንዳይሰሩ የአማራ ህዝብና መንግስት ተስማምተው ለአማራ ህዝባችን ደህንነት ሲባል ሊገደብ ይገባል፡፡

ማንኛውም የአማራ ህዝብ ፀጉረ ልውጥ የሆነ ለማኝ፣ እብድ፣ ቄስ ወይም መነኩሴ መስለው በየአካባቢው ለመረጃ ስራ የተሰማሩትን ህዝቡን እንዲከታተል በመላ አማራ የማንቃት ስራ መስራት ህዝባችን ተደራጅቶ ራስን የመከላከል ስራ እንዲሰራ ማገዝ፡፡ ይህንን የምንለው ያለን መፍትሄ የትግራይ ህዝብን ከመጥላት አይደለም። ከህወሓት ሴራና ተንኮል ተነስተን ለአማራ ካለው ጥላቻ የተነሣ አሁን ገበሬ አዝመራ በሚሰበስብበት አማራ ካላጠፋን መተኛት አንችልም በማለት መላ የትግራይ ገበሬ አዲስ መሣሪያ ዕድሜና ፆታ ሳይለይ መሣሪያ በማስታጠቅ ፀረ አማራ ተሰለፍ ብሎ ሌት ተቀን በማሰልጠን ላይ ይገኛል። ለዚህ ነው የአማራ ህዝብ የዋህነትና እንቅልፍ ይብቃ፡፡ ራሳችን ለማዳን እና ለመከላከል ትግላችን ከውስጥ ወደ ውጭ ይሁን፡፡

6. ‹‹ወልቃይት ጠገዴ ትግራይም አማራም አይደለም ወልቃይት ራሱ የቻለ ህዝብ ነው›› በሚል የፈጠራ ታሪክ ህወሓት ሽርኵ አንዳንድ የወልቃይት ተወላጆች ለታሪክና ለማንነት ያልታደሉ ለሆዳቸው ያደሩ በጋብቻና በጥቅም ከትግራይ ባለስልጣን የተሳሰሩ ግማሽ ጐናቸው የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን አደራጅቶ ወደ ፌዴራል መንግስት ፌዴሬሽን ም/ቤት እንደ አዲስ ጥያቄ እንዲያቀርቡ በህወሓት ከፍተኛ በጀት ተመድቦ እንደሚንቀሳቀሱ ሚስጥሩን ደርሶናል፡፡ ሃሣቡ ደግሞ እጅግ መሰሪ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ማንነትና ታሪክ አልባ ከማስቀረት አልፎ ከሚወደው ህዝብ አማራ ነጥለው ለዘልአለም ዙፋን እንዲጠፋ ለማድረግ በሰፈራ የመጣ ከትግራይ ሕዝብ በወልቃይት ጠገዴ እኩል የመወሰን መብት የሚሰጥ እንደሆነ እና የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በትግራይ ተወላጆች ቁጥር ተበልጦ ቀጣይ ተመልሶ የትግራይ ማንነት እንዲያነሣ በማድረግ ለዘለዓለም የትግራይ ግዛት ለማስደረግ እንደሆነ ሴራው ገብቶናል፡፡ ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ በአግባቡ የማይመልስ መንግስትና ድርጅት ከሆነ አማራ ወሰኑ ተከዜ ነው ተከዜ መልስ በህግና በውዴታ ህወሓት የማይልስ ከሆነ አማራ በግድ የማስመለስ ወኔም አቋምም አለን፡፡ ህወሓት ብንነግረው ብንነግረው አልሰማም ካለ በእስክርቢቶና በወረቀት ልጠየቅነው መትረየስና ላውንቸር ታጥቆ አማራ መውጋት ነው መፍትሄድ ካለ እኛ ምንም ማድረግ አንችልም የተኛው አንበሣ መቀስቀስ ነው፡፡

ህወሓት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ብሔርተኝነት አለመመለሱ ከጊዜ በኋላ ውጤቱ ቀሪው ኃይል በታሪክ ሊነግረን ይሆናል፡፡ ህወሓት የአማራ ህዝብ ጥያቄ ላለመመለስ ጦርነት ከመረጠ በአማራ አሸናፊነት እንደሚደመደም አትጠራጠሩ፡፡ ህወሓት የአማራ ህዝብ ጥያቄ በሰላም ከመለሰ ግን አሸናፊም ተሸናፊም አይኖርም በኢትዮጵያዊነታችን በጋራ እንኖራለን፡፡ ለማንኛውም የአማራ ህዝባችን ራሱን ለማስከበር ይደራጅ፡፡

7. ሌላው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ተብሎ ተቀራርበን አማራዎች ከመመካከር ይልቅ በብዙ ቡድን እና ፓርቲ ተበትነን ህዝባችን ግራ ከማጋባት ከስሜትና ከአሉባልታ ነፃ ሁነን በሚያመሳስሉን ተቀራርበን በመስራት በሚያለያዩን ደግሞ ተከባብረን ልዩነታችን ወደ ህዝብ በማቅረብ ፈራጅና ዳኛ ህዝብ እንደሆነ አምነን ለአማራ ብሔርተኝነት ከልብ እንታገላለን፡፡
የአማራ ህዝብ የተለያዩና ብዙ ድርጅቶች ለችግራችን መፍትሄ አይደሉም፡፡ የአማራ ህዝብ የሚያስፈልገን አንድ ወይም ሁለት ጠንካራ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ብቻ ነው የሚያስፈልጉን እንዲህ ከሆነ ጉልበትም አቅምም እንዲፈጥ

ር አማራ ይረዳል፡፡
በመጨረሻ በምክንያት የተደገፈ የአማራ ብሔርተኝነት በማጠናከር በምክንያት የተደገፈ የአገር አንድነት እንድንመሰርት ከለውጥ የአመራር ኃይል ጐን በመሰለፍ ለሁላችን ኢትዮጵያዊያን ዘር ጐሣ ሳትል በእኩል ዓይን የምታስተናግድ አገር እስከምንፈጥር ጠንክረን እንታገላለን፡፡ ለውጡን እውን እንዲሆን አማራ በብሔር የደራጅ የማንነትና የወሰን ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ አማራ በብሔር ይደራጅ፡፡

ምንጭ፡ ጌታቸው ሽፈራው

መስከረም 08/01/2011 ዓ.ም