Author Archives: Kidane

ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

  ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ የሃዘን መግለጫ ኢትዮጵያ ሃገራችን ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ የጀመረችው የለውጥ ጉዞ ከጅምሩ ብዙ እንቅፋቶችና ውጣ ውረዶች የተጋረጡበት እንደሚሆንና የዚህ ሁሉ ችግር መንስኤ ደግሞ በአለፉት 27 የጭቆና እና የግፍ ዘመናት በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የተፈጸሙት እኩይ ተግባራት ድምር ውጤት መሆኑን ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን ይገነዘባል። ከዚህም በመነሳት የለውጥ ሃይሉ ለአለፈው አንድ አመት የወሰዳቸው አስደናቂ የለውጥ ውሳኔዎችና ተግባራት በእጀጉ የሚያኮሩና ...

Read More »

በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

ከጥንቱም ሌባ ሲሸሽ የዘረፈውን እያንጠባጠበና መውሰድ ያቃተውን እያበላሸ ነው! አበው “ተፈጥሮን ተመክሮ አያድነውም” እንዲሉ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር /ትህነግ/ በአለፉት 25 ዓመታት የኢትዮጵያን መንግስታዊ ስልጣን በብቸኝነት ከላይ እስከ ታች ይዞ በሃገርና በህዝብ ላይ የፈፀመው አይን ያወጣ ሃገራዊ ሌብነትና ዝርፊያ፣ ህዝባዊ እልቂትና ምስቅልቅል፣ ሃገራዊ ክህደትና ውርደት፣ አጠቃላይ ወንጀልና ሰቆቃ ለመረዳት ዛሬ በመንግስት የዜና ማሰራጫ አውታሮችን ብቻ የሚተላለፉ ምስክርነቶችን መመልከት በቂ ...

Read More »

የአቸናፊዎች ፍትሕ

የ“አሸናፊዎች ፍትህ”ና የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በአለማችን ሁሉም ማዕዘናት ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ በተለያዩ ዘመናትና ሁኔታዎች በተደረጉ ህልቆ መሳፍርት በሌላቸው ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊና፣ ኢኮኖሚያዊ ትግሎችና ፍትጊያዎች “አሸንፈው” ወደ ስልጣንና የሃይል ማማ ላይ የወጡ “አሸናፊ” ግለሰቦቸ፣ ቡድኖች፣ ወይም ህዝቦች ለ“ተሸናፊው” አካል የሚቸሩት ሁለገብ መሰተንግዶ ወይም “ፍትህ” በአይነቱ፣ በመጠኑም ሆነ በይዘቱ እንደዬ አግባቡ ቢለያይም (መለያየቱ እንደተጠበቀ ቢሆንም) በ“ዓለማቀፋዊ የፍትሃዊነት” መመዘኛዎች የእይታ አድማስ ውስጥ በመካተት ...

Read More »

ወያኔ የራያን ሕዝብ መሬት ለመዝረፍና ማንነቱን በሃይል ለመጨፍለቅ የምታደረገው አፈና ትግሉን በይበልጥ ያጠናክረዋል እንጅ አያስቆመውም።

ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ መግለጫ፣ ወያኔ የራያን ሕዝብ መሬት ለመዝረፍና ማንነቱን በሃይል ለመጨፍለቅ የምታደረገው አፈና ትግሉን በይበልጥ ያጠናክረዋል እንጅ አያስቆመውም። የትግራይ ሕዝብ ነፃ ግንባር (ትሕነግ) ዘርንና ቋንቋን መሰረት ባደርገ መንግስታዊ አወቃቀር የኢትዮጵያን ህዝብ የጫነችበት ቀንበር ከጀርባው ለማላቀቅ፣ ለሃያ ሰባት አመት ያደረገው እልክ አስጨራሽ ትግል ብዙ የደም ዋጋ ቢከፈልበትም፣ አሁን ለደረስንበት የሰላም ጮራ በመጠኑ ለማየት አብቅቶናል፣ ይህን የተጀምረው የእርቀ ሰላም ጉዞ ...

Read More »

‘ልሳነ ግፉአን’ የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ አዲስ አበባ ገብቷል _ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

  https://www.ena.et/?p=9846     ‘ልሳነ ግፉአን’ የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ አዲስ አበባ ገብቷል   አዲስ አበባ አምሌ 5/2010 መቀመጫውን ሰሜን አሜሪካን አድርጎ ለ16 ዓመታት በኢትዮጵያዊያን ሰብዓዊ መብት ዙሪያ ሲንቀሳቀስ የነበረው ‘ልሳነ ግፉአን’ የተሰኘው ድርጅት ኃላፊዎች አዲስ አበባ ገብተዋል። ድርጅቱ የኢትዮጵያዊያን መብት መነፈግን መነሻ በማድረግ በመሟገት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ለኢዜአ እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ወራት ...

Read More »

ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ስብዕና በቤተሰብ እይታ (በአብዩ በለው)

ግንቦት 4 ቀን 2010 ዓ ም ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ስብዕና በቤተሰብ እይታ (በአብዩ በለው) ዛሬ በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ የተሰዉበትን 150ኛ ዓመት ለመዘከር በተዘጋጀው ታሪካዊ ዝግጅት ላይ ለመታደም የተገኛችሁ – ክቡራን የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች፣ – የተከበሩት አንጋፋ ጋዜጠኛና ደራሲ ክቡር አቶ ተክሌ የኋላ፣ – የተከበርከው የአንድነት፣ የፍትህና፣ የዲሞክራሲ ታጋይና የሰላማዊ ትግል ...

Read More »