Welkait, Tegede and Tselemt.

ይድረስ ለጎንደር! ይድረስ ለኢትዮጵያ ህዝብ! በጎንደሬ መካከል ምርጫ የለም! የሞት ድግስ ተሰርዟል !

ጀግናው የጎንደር ህዝብ ሆይ!

“ድንበራችን ተከዜ ነው!” ያሉት ልጆችህ በወያኔ አረር እንደቅጠል የረገፉበት አንደኛ የሙት አመት በሚከበርበት ዋዜማ ጀምሮ የቀሪ
ልጆችህን ደም ዳግም ለማፍሰስ የበቀል ቢላውን የሚስለው የትግራይ ነፃ አውጭ አውሬ በምርጫ ስም ቀን ቆርጦ በልጆችህ ሬሳ ላይ
ከበሮ ሊደልቅ እነሆ እየጠበቀህ ይገኛል።

ወልቃይቴው እኔ “ጎንደሬ/አማራ ነኝ” በማለቱ፣ ጠገድቼው “ጠገዴ አንድ ነው!” በማለቱና፣ ጠለምቴው “ድንበራችን ተከዜ ነው!” በማለቱ
ብቻ በወያኔ ጥይት ሲደበደብ አብረህ ደምህን ያፈሰስክ፣ ሲታሰር እኩል የተቸነከርክ፣ ሲሰደድ ጨርቄን ማቄን ሳትል ዱር-ቤቴ ያልክ፤
ዛሬም ሆነ ነገ የቅማንት ወንድምህ ሲከፍው አብረህ የምትከፍው፣ አማራው ሲሳደድ አብረህ የምትሳደደው አንተ ጎንደሬው ባለማተቡ
ነህ።

ዛሬ ሾተላዩ ዳግም የንፁሃን ልጆችህን ደም ሊመጥ በደጅህ አሰፍስፎ ይገኛል። ቅማንት መስሎና አክሎ የጎንደርን መሬት ሊካፈል የመጣውና
አማራ ይውጣ እያለ የሚደነፋው የትግሬ ወራሪ እንጂ ጎንደሬ ወንድምህ አይደለም። አማራን መስሎና አክሎ ቅማንት መጣብህ እያለ
ወንድምህ ላይ እጅህን እንድታነሳ የሚነዘንዝህ ወያኔ እንጂ አብሮ አደግ ወንድምህ አይደለም። Read In PDF

Exit mobile version