ወያኔን ከስልጣን ማስወገድ እንጂ መደራደር መፍትሄ እያመጣም

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያስታውሰው በእንግሊዞችና በአሜሪካኖች ተቀነባብሮ በአቶ ኽርማን ኮሆን
አጋፋሪነት(medioter) ከሦስት ብሄራዊ ድርጅቶች(EPLF, TPLF ና OLF) ጋር በ1991 በሎንዶን የተደረገዉ ስብሰባ በዋናነት
ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት ሃይሎችን ለስልጣን የሚያበቃና ጥቅም የሚያስጠብቅ ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሃገራችን
እንድትበታተን የሚያስችል ስትራተጂ የተነደፈበት የኢትዮጵያውያን የጨለማ ቀን ነው።

ከላይ በተጠቀሱት ተገንጣይና አስገንጣይ ድርጅቶች በሽፍትነት ዘመናቸው ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ አንግበው
ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ በኋላ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የተጠላዉንና እየተዳከመ የመጣዉን ወታደራዊ እምባገነን
ሥርዓትን አስወግደው በሃይል ስልጣን ላይ ተቆናጠጡ። ለይስሙላም ከነርሱ ዉጪ ማንንም ኢትዮጵያዊ ፖለቲካ ድርጀት፥
የሙያ ማሕበራት፥የመምህራን ማህበር፥ የሰራተኛ ማህበር፥ የተማሪዎች ማህበር፥የሃይማኖት መሪዎች፥ አርሶ ኣደሮች፥
የታሪክ ተመራማሪዎች፥ ታዋቂ ግለሰቦችና ያአገር ሽማግሌዎችን ያላሳተፈ የሽግግር መንግሥት አቋቋምን አሉ። ለነርሱ
በሚመችና የታገሉለትን ዓላማ የሚመጥን፥ የሃገሪቱን ዓንድነት የሚንድ፥የሕዝቡን ለዓላዊነትን የማያከብርና የቋንቋ
ፈደራሊዝምን በዋናነት የአገሪቱ የአሰተዳደር ስርዓት እንዲሆን ሕገመንግስት አርቅቀው ራሳቸው አፅድቀው የሃገሪቱ ሕገ
መንግስት ነው ብለው ሕዝቡ ያልመከረበት፥ያልተሳተፈበት፥ ዕዉንታዉን ያልሰጠበትና፥ያለዉዴታ በግዴታ ተግባራዊ
እንዲሆን አደረጉ። Read In PDF