ልሳነ ግፉዓን “ከዚህ ወዴት” በሚለው ጭብጥ ዙሪያ የመወያያ ሃሳብ ስለማቅረብ

በቅድሚያ በእጀጉ የምኮራበትንና በፈቃደኝነት የማገለግለውን ድርጀት መስርታችሁ፣ በብዙ እንግልትና መሰናክል ውስጥ አልፋችሁ፣
ከልሳነ ግፉዓን ጋር በይፋ መስራት እስከ ጀመርኩብት 2010 ድረስ የድርጀቱን ህልውና፣ ጥራትና፣ ብቃት በአስተማማኝ ሁኔታ ጠብቃችሁ
ላቆያችሁኝ የልሳነ ግፉዓን አመራሮችና መስራች አባላት የአክብሮት ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ።

እኔ ወደ ሰሜን አሜሪካን በስደት ከመጣሁበት ከ2010 ጀምሮ ያመንኩትና በይፋ አብሬው የሰራሁት ድርጀት ቢኖር ልሳነ ግፉዓን ብቻአን
ብቻ ነው። ምክንያቱም ልሳነ ግፉዓን የቆመለት አላማና የሚከተለው የትግል ስልት/strategy/፣ የመሪዎቹና የአባላቱ ታማኝነትና፣ ጨዋነት፣
ፋሽስቱንና ተስፋፊውን የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ድርጅት አምርሮ ለመታገል ያላቸው ብቃትና ቁርጠኝነት፣ ይልቁንም ለህወሃት የስለላ
መዋቅርና ለተመሳሳይ ሰርጎ ገቦች በፍፁም የማይከፈትና ለዘለዓለሙ የተዘጋ የምስጢር አጠባብቅ ዘዴ ባለቤት መሆናቸውን ማረጋገጥ
በመቻሌ ነበር። Read In PDF

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*